በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍጋኒስታን በወታደራዊ አካዳሚ በደረሰ ጥቃት አሥራ አንድ ሰዎች ተገደሉ


አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በሚገኝ አንድ ወታደታዊ አካዳሚ በደረሰ ጥቃት፣ 11 የአፍጋኒስታን ብሔራዊ ጦር ኃይል አባላት ሲገደሉ ሌሎች 16 መቁሰላተው ተገለፀ።

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በሚገኝ አንድ ወታደታዊ አካዳሚ በደረሰ ጥቃት፣ 11 የአፍጋኒስታን ብሔራዊ ጦር ኃይል አባላት ሲገደሉ ሌሎች 16 መቁሰላተው ተገለፀ።

ጥቃቱ በአካዳሚዎ ላይ ሳይሆን አካዳሚውን በሚጠብቁ ወታደሮች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር፣ የአፍጋኒስታን መከላከያ ሚኒስቴር ቃልአባይ ዳወላተ ዋዚሪ አስታውቀዋል። ውጊያው፣ በማርሻል ፋሂም ብሔራዊ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ከሰዓት በኋላም ቀጥሎ መዋሉ ተሰምቷል።

የመከላከያ ሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ ዋዚሪ እንደተናገሩት፣ ጥቃቱን አምስት አጥፍቶ ጠፊዎች ናቸው ያደረሱት። ሁለቱ፣ በአካዳሚው መግቢያ በራፍ ላይ የታጠቁትን ቦምብ አፈንድተው ሲጋዩ፣ ወደ ቅጥር ጊቢው ለመግባት ከሞከሩት ከሦስቱ መካከል፣ ሁለቱ በብሔራዊው ጦር ተገድለው አንዱ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጧል።

ራሱን ስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ነውጠኛ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነት መውሰዱንም፣ “አማቅ” በተሰኘው ዜና አውታሩ አማካኝነት ይፋ አድራል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG