በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ማዕድን አውጪዎች የያዘ አሳንሰር ወድቆ 11 ሰዎች ሞቱ


በደቡብ አፍሪካ በሰሜናዊ ሩስተንበርግ ከተማ የሚገኝ  የማዕድን ማውጫ
በደቡብ አፍሪካ በሰሜናዊ ሩስተንበርግ ከተማ የሚገኝ  የማዕድን ማውጫ

በደቡብ አፍሪካ በሰሜናዊ ሩስተንበርግ ከተማ በሚገኝ የማዕድን ማውጫ ትናንት ማክሰኞ በደረሰ አደጋ 11 ሰዎች ሲሞቱ 75 ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ፡፡

አደጋው የደረሰው በፕላቲነም ማዕድን ማውጫው ውስጥ 200 ሜትሮች ወይም 656 ጫማ ከፍታ ላይ የነበረ አንድ የሰዎች ማመላለሻ (አሳንሰር) ሠራተኞቹን ይዞ በድንገት በመውደቁ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በአደጋው ከቆሰሉት መካከል ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው 14 ሰዎች ሆስፒታል ገብተው እየታከሙ መሆኑን የማዕድን ማውጫውን ሥራ አስፈጻሚ ኒኮ ሙለርን ጠቅሶ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

አሳንሰሩ በምን ምክንያት እንደሆነ ምርመራ መጀመሩንም ዘገባው አመልክቷል፡፡ ወደፕላቲነም ማዕድኑ ስፍራ በሚወስደው የአንድ ኪሎ ሜትር ጥልቀት ማዕድን ቆፋሪዎችን የሚያጓጉዘው ግዙፉ ባለሦስት ፎቅ አሳንሰር ቁልቁል ተውዘግዝጎ የወደቀው የስራ ፈረቃቸውን ጨርሰው የሚወጡ ሠራተኞችን አሳፍሮ በመውጣት ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዓለም ትልቋ የፕላቲነም አምራች በሆነችው በደቡብ አፍሪካ ስትሆን ማዕድን ማውጫዎች ውስጥ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ እየቀነሰ መምጣቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

እ.ኤ.አ. ባለፈው 2022 ዓም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በደረሱ የማዕድን ማውጫ አደጋዎች 49 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ቁጥሩ ከቀደመው ዓመት በ74 ከመቶ ቀንሷል።

እ.ኤ.አ. በ2000 ዓመተ ምሕረት በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ማውጫዎች በደረሱ አደጋዎች ቁጥራቸው ወደ 300 የሚጠጋ ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከዚያ ወዲህ ቁጥሩ በተከታታይ እየቀነሰ መምጣቱን ከመንግሥት የተገኙ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG