በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዲሞክራሲዋ ጥንካሬ የሚፈተንበት ምርጫ በዛምቢያ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዛምቢያ ከነገ ወዲያ ሀሙስ ምርጫ ታካሂዳለች። በዚህ ምርጫ ያቺ ሀገር በአፍሪካ አህጉር በተረጋጋ ዲሞክራሲያዊ ስርዓታቸው ቁንጮ ከሆኑት ሃገሮች ተርታ የያዘችው ስፍራ እየተፈተነበት ይገኛል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉ በድጋሚ ለመመረጥ በዕጩነት ቀርበዋል። ከሌላው ዕጩ ከአንጋፋው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሃካዪንዴ ሂቺሌማ ጋር ብርቱ ፉክክር እንደሚኖር ከወዲሁ ተጠብቋል። አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነም ምርጫው የፖለቲካ ቀውስ ሊቀሰቀስ ይችላል እያሉ ነው።

ፕሬዚዳንት ሉንጉን የሚነቅፉዋቸው ወገኖች አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮችን በመዝጋት፣ ተቃዋሚዎችን በማሰር እና የሚተቿቸውን ሰዎች በማሳደድ ዲሞክራሲያዊ መብቶችን እያፈኑ ናቸው ይሏቸዋል።

ሂዩማን ራይትስ ባለፈው ሰኔ ባወጣው ሪፖርቱ ሉንጉ ዛምቢያን ወደሰብዓዊ መብት ቀውስ አፋፍ እየወሰዱዋት ናቸው ብሎ መንቀፉ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG