በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምርጫ ውጤቶች የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ በሰፊ ልዩነት እየመራ መሆኑን አመላከቱ


ሰባ አምስት ከመቶ የሚሆነው ድምጽ ተቆጥሯል ኢህአዴግ ይመራል፤ ከታዋቂ ተቃዋሚዎች እስካሁን ያሸንፈ የለም

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ማምሻውን የመጀመሪያ ደረጃ የምርጫ ውጤቶችን ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ገዥው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በሰፊ ልዩነት እየመራ መሆኑ በጊዚያዊ የምርጫ ውጤቶቹ ተመልክቷል።

በመላው ሀገሪቱ እሁድለት የተሰጠው ድምጽ 75 ከመቶ የሚሆነው እንደተቆጠረ የምርጫ ቦርድ ገልጾ፤ በጠቅላላ ውጤቱ ገዥው ፓርቲ በሰፊ ልዩነት እየመራ መሆኑን አውጇል።

የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር መርጋ በቃና ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች ሰኞለት በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ከሚገኙ መቀመጫዎች ኢህአዴግ 20ውን ሲያሸንፍ መድረክ በአንዱ አሸንፏል። የተቀሩት ሁለት መቀመጫዎች ቆጠራቸው እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የተቃዋሚ መሪዎች ሁኔታው በገዥው ፓርቲ ዘንድ ፍጹም አሸናፊ ለመሆን የተደረገው ዘመቻ አካል ነው ብለዋል። ከተቃዋሚዎች ጎራ አዲስ አበባ ላይ አንድ የመድረክ አባል ካሸነፈበት የምርጫ ውጤት በስተቀር ታዋቂ የተቃዋሚ መሪዎች እስካሁን እንዳላሸነፉ ይናገራሉ።

(የአማርኛው ዝግጅት ክፍልን የቀጥታ ዘገባ ለማዳመጥ በገጹ በስተቀኝ ያምሩ)

XS
SM
MD
LG