በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫዎች እየተካሄዱ ነው


መራጯ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭብል አድረው
መራጯ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭብል አድረው

በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ውስጥ በዛሬው እለት በመካሄድ ላይ በሚገኘው ምርጫ፣ በምርጫ ሂደት ላይ ስላለው ተአማኒነትና ተቀባይነት ፍንጭ የሚሰጥ ሲሆን፣ የበርካታ አወዛጋቢ ፖሊሲዎች ተቀባይነት የሚፈቱነበት እንደሆነም ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው የኒውጀርሲና የቨርጂኒያ ገዢዎችን ምርጫ ውድድር ጨምሮ፣ ከንቲባዎች፣ የወረዳ ምክር ቤት፣ እና የትምህርት ቤት ቦርድ አባላት ምርጫ፣ በበርካታ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህ ምርጫ አስቀድሞ የሚፈተነው ሪፐብሊካኖች በሚያስተዳድሯቸው አንዳንድ ክፍለ ግዛቶች፣ በመራጮች ተሳትፎ ላይ ተጥለዋል የተባሉት ገደቦች እና የምርጫ ተአማኒነት ናቸው፡፡

ካለፈው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ፣ ለረጅም ጊዜ የተነዙ የተሳሳቱ መረጃዎች ትክክለኛ መሆን አለመሆናቸው የሚረጋገጥበት ጊዜ መሆኑንም ባለሥልጣናት ገልጸዋል፡፡

ሪፐብሊካኖች በሚያስተዳድድሯቸው ግዛቶች ባወጧቸው ጥብቅ ህጎች የተነሳ፣ በተወሰኑ ግዛቶች ያሉ መራጮች ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችልም ተመልክቷል፡፡

የምርጫ አስጸፈጻሚ ባለሥልጣናት፣ እስከዛሬ እንደነበረው ደህንነቱና አስተማማኝነቱ የተጠበቀ ፍትሃዊ ምርጫ በማድረግ፣ ካለፈው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወዲህ፣ ጥርጣሬ ያደረባቸውን መራጮች ለማሳመንና፣ ለመጭው ዓመት፣ የእኩሌታው ምርጫ ዘመን ፣ እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG