በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ውስጥ በህንጻ ተደርምሶ 8 ሰዎች ሲሞቱ 23 ሰዎች ቆስለዋል


የንግድ መናኻሪያ በሆነቸው የናይጄሪያ ከተማ ሌጎስ ውስጥ የሚገኝ አንድ ባለ 23 ፎቅ ህንጻ ተደርምሶ 8 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 23 ደግሞ መቁሰላቸው ተነገረ፡፡
የንግድ መናኻሪያ በሆነቸው የናይጄሪያ ከተማ ሌጎስ ውስጥ የሚገኝ አንድ ባለ 23 ፎቅ ህንጻ ተደርምሶ 8 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 23 ደግሞ መቁሰላቸው ተነገረ፡፡

የንግድ መናኻሪያ በሆነቸው የናይጄሪያ ከተማ ሌጎስ ውስጥ የሚገኝ አንድ ባለ 23 ፎቅ ህንጻ ተደርምሶ 8 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 23 ደግሞ መቁሰላቸው ተነገረ፡፡ ህንጻው የወደቀው ትናንት እሁድ ምሽቱን ኡቡት ሜታ በተባለው አካባቢ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ባላፈው ጥር ወር፣ አንድ የቤተክርስቲያን ህንጻ ላይ በተከሰተ መደርመስ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ተነገሯል፡፡ ናይጄሪያ ውስጥ የፎቆችና ህንጻዎች መደርመስ የተለመደ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ባለፈው ህዳር በተመሳሳይ ሁኔታ በተደረመሰ ህንጻ 45 ሰዎች ከሞቱ ወዲህ የህንጻዎች ግንባታ ደረጃቸው የጠበቁ ስለመሆናቸው ጥያቄ ማስነሳት መጀመራቸው ተነግሯል፡፡

ናይጄሪያ ውስጥ እኤአ ከ2005 ጀምሮ ቢያንስ 152 ህንጻዎች መደርመሳቸውን አንድ በሌጎስ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ተማራማሪ አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG