በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ኢድ ሙባረክ" ፕሬዚዳንት ትረማፕ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረማፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረማፕ

"ከሜላንያ ጋር ሆነን የሞቀ የኢድ አልፈጥር ሰላምታ እናስተላልፋለን" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረማፕ የበዓሉን መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተቀደሰው የሮማድን ፆም ማብቂይ ላይ ሙስሊሞች ኢድን በፀሎትና በማሰላሰል ያከብሩታል።

ይህ የተቀደሰ ዕለት በዩናይትድ ስቴትስና በዓለም ዙርያ ላሉት ሙስሊሞች ሁሉ በድኅነት የሚኖሩትን የመርዳት ተግባሩን ለማደስ፣ በአምላክ ላይ ያላቸውን ዕምነት ለማጠናከር፣ በዕምነታቸው ለመፅናት እንዲሁም ከሌሎች ጋር ግንኙነታቸውን ለማዳበር ዕድል ይሰጣቸዋል።

ይህን በዓል ለሚያከብሩት ሁሉ ደስታና ሰላም እንደሚያመላቸው ተስፍ እናደርጋለን። በዓለም ዙሪያ ያሉት ማኅበረሰቦች የአምላክን የበዛ የፍቅር መባረክ፣ ይቅር ባይነትና በጎነት እንዲሰማቸው እንፀልያለን ሲሉ ፕሬዚዳንት ትረምፕ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ "ዒድ ሙባረክ" ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG