መንግሥት በየጊዜው የሚነሱ ግጭቶችን በውይይት በመፍታት፣ በመላ ሀገሪቱ ሰላምና ጸጥታን በማስፈን፣ ለሽግግር ፍትሕ አፈጻጸም ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አሳስቧል፡፡
ይህም፣ ሂደቱ አካታች፣ ተዓማኒ እና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን የሚያስችል እንደሆነ የኢሰመኮ የሕግ እና የፖሊሲ ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ታሪኳ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት፣ በሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ፣ ተጎጂዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር ምክክር በማድረግ ባለ 90 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርገዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም