በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለትግራይ እርዳታ እንዲፋጠን የመብቶች ኮሚሽኑ አሳሰበ


በህወሓትም በፌዴራልም መንግሥት ወገኖች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ገለጸ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ፣ ችግሩ በወታደራዊ አማራጭ እንደማይፈታ ሁሉም ወገኖች እስካሁን የተረዱ አይመስለኝም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መረጋጋት እና አንድነት ለአካባቢያዊ መረጋጋት እና አንድነት በጣም አስፈላጊ ምሰሶ መሆኑን መገንዘብ አለብን ያሉት ጉቴሬሽ ይህ ግጭት ከኢትዮጵያ ድንበሮች አልፎ የሚሄድ ተፅዕኖ ሊኖረው የሚችል መሆኑ በጣም ያሳስበናል ሲሉም ተናግረዋል። ኢሰመኮ ቅዳሜ እለት ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡

በኮሚሽኑ መግለጫም ይሁን በተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸኃፊ ሀሳብ ዙሪያ ከህወሓትም ይሁን ከፌዴራል መንግሥት እስካሁን የተሰጠ ምላሽም የለም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ለትግራይ እርዳታ እንዲፋጠን የመብቶች ኮሚሽኑ አሳሰበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:52 0:00



XS
SM
MD
LG