በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዳያገረሽ ሁሉም ወገን የድርሻውን እንዲወጣ ኢሰመኮ ጠየቀ


የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዳያገረሽ ሁሉም ወገን የድርሻውን እንዲወጣ ኢሰመኮ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:38 0:00

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዳያገረሽ ሁሉም ወገን የድርሻውን እንዲወጣ ኢሰመኮ ጠየቀ

ጋብ ብሎ የቆየው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሊያገረሽ እንደሚችል ሥጋቱን የገለፀው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች፣ የሲቪል ማኅበራት፣ መገናኛ ብዙሃን፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው እና ሌሎች አካላት ለሰላማዊ መፍትሔ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣

"ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተለያዩ ወገኖች የሚደመጡ መግለጫዎች ግጭትን መልሶ የማገርሸት አደጋ የሚያመለክቱ ናቸው" ብለዋል።

ኮሚሽኑ የሰላም ጥሪ ያቀረበውም ያለፈው እንዳይደገም ከመስጋት በመነጨ መሆኑን ዶ/ር ዳንኤል ተናግረዋል።

“ጥሪ ያቀረብነው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ባለፉት በርካታ ወራት ያስከተለውን ቀውስ ከማወቃችን የተነሣ ነው” ብለዋል።

በኮሚሽኑ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን አነጋግረን ያጠናቀርነውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG