በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢሰመኮ ሪፖርት በትግራይ ክልል


በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት እና የቀድሞ መስተዳደርን መፍረስ ተከትሎ ፆታዊ ጥቃቶች መፈፀማቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን /ኢሰመኮ/ ከመቀሌ፣ ከአይደር፣ ከአዲግራት እና ከውቅሮ ሆስፒታሎች አገኘሁ ባለው መረጃ መሰረት ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 108 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች እንደተፈፀመባቸው ትናንት ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

በበርካታ የትግራይ አካባቢዎች አሁንም ወደ መደበኛ ሥራ ያልተመለሰው የመሰረት ልማት፣ የማኅበራዊ እና የአስተዳደር አገልግሎት የአካባቢውን ነዋሪዎችና እና ተፈናቃዮች ለተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እያጋለጠ መሆኑን አስታውቋል።

2 ነጥብ3 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የኢሰመኮ ሪፖርት በትግራይ ክልል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:38 0:00


XS
SM
MD
LG