በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ ክልል በስምንት ወራት ውስጥ 138 ሰዎች እንደተገደሉ ኢሰመኮ አስታወቀ


በጋምቤላ ክልል በስምንት ወራት ውስጥ 138 ሰዎች እንደተገደሉ ኢሰመኮ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:15 0:00

በጋምቤላ ክልል በስምንት ወራት ውስጥ 138 ሰዎች እንደተገደሉ ኢሰመኮ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በጋምቤላ ክልል ከግንቦት 2015 እስከ ጥር 2016 ዓ.ም ድረስ በተከሠቱ ግጭቶች፣ ቢያንስ 138 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፣ በግጭቱ የንብረት ውድመት እና ዘረፋ መፈጸሙንም በምርመራው ማረጋገጡን ጠቅሷል።
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አቤል አዳነ፣ ስለ መግለጫው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ በግጭቱ በጋምቤላ ክልል የሚኖሩ ስደተኞችም እንደተሳተፉ ተናግረዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጠው የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በበኩሉ፣ ባለፈው ዓመት ከግንቦት እስከ ነሓሴ ወራት ድረስ አጋጥሟል ባለው ግጭት፣ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱን አምኖ፣ መጠኑን ግን አልገለጸም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG