የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በጋምቤላ ክልል ከግንቦት 2015 እስከ ጥር 2016 ዓ.ም ድረስ በተከሠቱ ግጭቶች፣ ቢያንስ 138 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፣ በግጭቱ የንብረት ውድመት እና ዘረፋ መፈጸሙንም በምርመራው ማረጋገጡን ጠቅሷል።
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አቤል አዳነ፣ ስለ መግለጫው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ በግጭቱ በጋምቤላ ክልል የሚኖሩ ስደተኞችም እንደተሳተፉ ተናግረዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጠው የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በበኩሉ፣ ባለፈው ዓመት ከግንቦት እስከ ነሓሴ ወራት ድረስ አጋጥሟል ባለው ግጭት፣ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱን አምኖ፣ መጠኑን ግን አልገለጸም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ማርች 14, 2025
በአፍሪካ የኅይል አቅርቦት ላይ ያተኮረውና በዋሽንግተን ዲሲ የተካሔደው ጉባኤ
-
ማርች 14, 2025
የኢትዮጵያውያት ሴቶች ጥያቄ ምንድን ነው? - የአድማጭ ተመልካቾች አስተያየት
-
ማርች 13, 2025
አርቲስት አንዱዓለም ጎሣ ተጨማሪ 13 ቀናትን በእስር እንዲቆይ ፍርድ ቤት ፈቀደ
-
ማርች 13, 2025
ሩሲያ የተቆጣጠረቻቸውን የዩክሬን ግዛቶች እንደያዘች መቀጠል ትሻለች