በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሰመኮ ባለፉት ስድስት ወራት ቢያንስ 161 ሲቪሎች መገደላቸውን አስታወቀ


ኢሰመኮ ባለፉት ስድስት ወራት ቢያንስ 161 ሲቪሎች መገደላቸውን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:51 0:00

ኢሰመኮ ባለፉት ስድስት ወራት ቢያንስ 161 ሲቪሎች መገደላቸውን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፉት ስድስት ወራት 161 ሲቪሎች መገደላቸውን ይፋ አደረገ። ለአማራ እና ለኦሮሚያ ክልሎች የግጭት ተሳታፊዎች የተኩስ አቁም ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ፣ ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው ሪፖርት፣ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ፣ ቢያንስ 161 ሲቪሎች፥ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ በዐማራ ታጣቂዎች፣ እንዲሁም “ማንነታቸው ያልታወቀ” ባላቸው ታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጿል፡፡

ካለፈው ታኅሣሥ ወር አጋማሽ አንሥቶ፣ በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ አካባቢዎች እንደተፈጸሙ ኮሚሽኑ፣ ከዘረዘራቸው ከሕግ ውጭ ግድያ እና የሲቪል ሰዎች ሞት ሕይወታቸው ካለፉት ውስጥ፡- 36 ሰዎች በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች፣ 68 ሰዎች በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች፣ 25 ሰዎች በአማራ የፋኖ ታጣቂዎች፣ እንዲሁም 32 ሰዎች “ማንነታቸው ያልታወቁ” ባላቸው ኀይሎች መገደላቸውን ሪፖርቱ ያትታል፡፡

በግጭት ዐውድ ውስጥ እና ከግጭት ዐውድ ውጭ ከሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መካከል፡- የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እና ዘረፋ፤ የዘፈቀደ፣ የጅምላ እና የተራዘመ እስራት እና የተፋጠነ ፍትሕ ዕጦት፤ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ እና የሀገር ውስጥ መፈናቀል፣ እጅግ አሳሳቢ ኾነው መቀጠላቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።

የግጭት ተሳታፊዎች በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች፣ ሰብአዊ መብቶችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ፣ በሲቪል ሰዎች ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ጥቃት ከማድረስ እንዲቆጠቡ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ ሁሉንም የትጥቅ ግጭቶች፣ በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምንና የሰብአዊ መብቶች መከበርን ማረጋገጥ እንደሚገባም አስገንዝቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG