በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል-ኢሰመኮ


በአርባ ምንጭ ዙሪያ ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል-ኢሰመኮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል-ኢሰመኮ

ከልዩ ወረዳ ጥያቄ ጋራ በተያያዘ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ባለፈው ጥቅምት ተከስቶ በነበረው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች መገደላቸውን፣ መቁሰላቸውንና መፈናቀላቸውን የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አስታወቆ በአከባቢው አሁንም ውጥረት መኖሩን በመጥቀስ ከመባባሱ በፊት አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርቧል።

በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሥር የሚገኙትን ኤልጎ፣ ወዘቃ፣ ደምብሌ እና ጫሞ 01 የተባሉ አራት ቀበሌዎች ከጋሞ ዞን በመውጣት በልዩ ወረዳነት ለመደራጀት በተለያየ ጊዜ ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸውንና ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ጥያቄውን ተከትሎ የተፈጠረው ውዝግብ መባባሱን ኢሰመኮ አስረድቷል።

በጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. በወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለ አንድ ግለሰብ በተያዘበት እና በቁጥጥር ሥር በነበረበት ወቅት በተፈጸመበት ድብደባ መሞቱ ደግሞ ውዝግቡን ይበልጥ እንዳባባሰው አመልክቷል።

በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በተለይም ከአካባቢያዊ አስተዳደር እና ከመዋቅር ጋር በተያያዘ ነዋሪዎች ጥያቄ ማነሳት ከጀመሩበት ወቅት አንስቶ የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ውትወታ ሲያደርግ መቆየቱን ኢሰመኮ አስታውሷል።

ኮሚሽኑ በአካባቢው እየተፈጸሙ ነው ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገሩ፣ የተፈጠሩ አለመግባባቶች ሕጋዊና ሰላማዊ መንገድን ተከትለው እንዲፈቱ ለፌዴራልና ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥታት ጥሪ አቅርቧል።

ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች በቂ የሆነ አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ እንዲቀርብና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰው በዘላቂነት የሚቋቋሙበት ሁኔታ እንዲመቻችም አሳስቧል። ከጋሞ ዞን አስተዳደር እና ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ተጨማሪ አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG