አዲስ አበባ —
የምርጫ 2013 ዋና አጀንዳ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ጉዳይ እንዲሆን የሲቪክ ማኅበራት ድርጅቶች ህብረትና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአንድነት እንደሚሰሩ ተገለጸ። ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ሁሉን አቀፍ እንዲሆንም ብርቱ ሥራ ይጠብቃቸዋል ተባለ።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ህብረትና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ ባዘጋጁት የአንድ ቀን የምክክር መድረክ ከኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ድርጅቶችና ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አኳያ በዘንድሮ ምርጫ ትኩረታቸው ምን መሆን እንዳለበት መክረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡