በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት ትጥቅ የፈቱ የቀድሞ ተዋጊዋችን በቅርበት እንዲከታተል ተጠየቀ


መንግሥት ትጥቅ የፈቱ የቀድሞ ተዋጊዋችን በቅርበት እንዲከታተል ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:49 0:00

መንግሥት ትጥቅ የፈቱ የቀድሞ ተዋጊዋችን በቅርበት እንዲከታተል ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በአገሪቱ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ሒደት መንግሥት በቅርበት እንዲከታተል ጠየቀ፡፡

ኢሰመጉ፣ ትላንት ኀሙስ መግለጫውን ያወጣው፣ ሰሞኑን፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ፣ ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ፣ ስምንት ሰዎች በጥይት መገደላቸውንና 16 ሰዎች መቁሰላቸውን፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት አገኘኹት ያለውን መረጃ በመጥቀስ ነው፡፡

ዛሬ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ ያደረጉት፣ በኮሚሽኑ የአሶሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ጉርሜሳ በፋጣ፣ ለጥቃቱ ተጠያቂዎቹ፣ ጫካ የነበሩና በቅርቡ ከመንግሥት ጋራ እርቅ ፈጽመው ወደ ከተማው የገቡ የጉምዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ናቸው፤ ብለዋል፡፡

ሓላፊው አያይዘውም፣ መንግሥት፣ ታጣቂ ኃይሎችን ትጥቅ የማስፈታት እና መልሶ የማቋቋም ሥራ ሲሠራ፣ በተጎጂ አካባቢዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መከታተል፣ የሰብአዊ መብቶችን ጥሰት ለመከላከል እንደሚያስችል አመልክተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG