በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብፃዊያን አብዮትና የሙባረክ ስንብት


የግብፅ ሕዝብ በፅናትና በሥነ-ሥርዓት በመራው ቁጣው የሰላሣ ዓመት ፕሬዚዳንቱን ከቢሮ አስወገደ፡፡

ሞሐመድ ጃማሊ የሚባል አንድ ቱኒዝያዊ ዴይሊኤምራልድ ለተሰኘ ዌብሣይት አዘጋጅ እንዲህ ሲል ፃፈ፡፡

"እነሆ ቱኒዝያ እገኛለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ ቱኒዚያ የት እንደምትገኝ ማብራራት ነበረብኝ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከእንዲህ ዓይነቱ ማብራሪያ አረፍኩ፡፡ ሃገሬ አምባገነኖቿን አሽቀንጥራ ጥላ የአብዮት ሰደድ ግብፅን ጨምሮ በድፍን የዐረብ ዓለም ይቀጣጠል ዘንድ መነሻ ሆናለችና፡፡"

የዴይሊኤምራልድ ዶት ኮም አዘጋጅ የካይሮን አደባባዮች ድንገት በሆታ የናጠው የሆስኒ ሙባረክ ሥልጣን መልቀቅ ወሬ በተናፈሰ በሁለት ሰከንዶች ውስጥ የሞሐመድ ጃማሊን ደብዳቤ ለሕትመት አበቃው፡፡

ታሕሣስ ስምንት ቀን 2003 ዓ.ም ሲዲ ቦውዚድ በተባለች አንዲት የቱኒዝያ ከተማ ፍራፍሬ ቸርችሮ ቤተሰቡን ማስተዳደር የተሣነው ሞሐመድ ቡዛዚ የቀለም ማቅጠኛ አኳራጅ እላዩ ላይ አርከፍክፎ በከተማይቱ ማዘጋጃ ቤት ደጃፍ እራሱን በእሳት አጋየ፡፡ ለዚህ የድፍረት አድራጎቱ በደረሰበት ከባድ ቃጠሎ ምክንያት ወደሆስፒታል ከመወሰዱ ይልቅ ከባድ የፖሊስ ድብደባ ተከተለው፡፡

ይህ የቦዛዚ የብስጭትና ተስፋ የመቁረጥ አድራጎት በሃገሪቱ የተንሠራፋው የከበደ ድህነት፣ የኑሮው ደረጃ መውደቅ፣ የፖሊስ አጉራ ዘለልነትና እብሪት፣ የተስፋፋው ሥራ ማጣት፣ የሰብዓዊ መብቶች መረገጥ እና ብልሽትሽት ያለው የኑሮ ቅጥ ማጣት መገለጫ ነበር፡፡

ሥልጣን የሙጥኝ ብለው የኖሩትን የረጅም ዓመታቱን አምባገነን ዚን ኤል አቤዲን ቤን አሊን ጥር 6 ቀን 2003 ዓ.ም አገር አስጥሎ ያበረረው የታኅሣስ ስምንቱ የቱኒዝያዊያን ቁጣ በዚያች በሲዲ ቦውዚድ ተፀነሰ፤ እናም እንዲያ ገንኖ በታሪክ ምዕራፍ ሆኖ እስኪሠፍር ታላቅ ሕዝባዊ አመፅ ሆነ፡፡

በዚያ የቱኒዝያ ሕዝብ ምሬት አመፅና ድል የተነሣሱ ሃያ ሺህ የሚሆኑ ግብፃዊያን ጥር 17 ቀን 2003 ዓ.ም በዕለተ-ማክሰኞ ልክ የዛሬ 17 ቀን ወደ ካይሮና ሌሎችም ከተሞች ጎዳናዎች ፈሰሱና በግብፅ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ፀረ-መንግሥት ሠልፍ አደረጉ፡፡ .....

ያለፉ 17 ቀናት እያንዳንዳቸው በታሪክ የተሞሉ ሆነው አለፉ፤ ዐርብ፣ የካቲት 4 ቀን በሕዝባዊው ቁጣ ውስጥ የተሾሙት በግብፅ ታሪክ አዲሱ ምክትል ፕሬዚዳንት ኦማር ሱሌይማን የሙባረክን ሥልጣን መልቀቅ ከቤተመንግሥት በቀጥታ ባደረጉት ንግግር አወጁ፡፡ ካይሮ በሆታ ተናጠች፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG