በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍልስጥዔማዊያን መፈናቀል 'ቀይ መሥመር ነው' – ሲሲ


ፎቶ ፋይል፦ የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ
ፎቶ ፋይል፦ የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ በእሥራኤልና በሐማስ መካከል የተደረሰውን ተኩስ የማቆም ስምምነት ትናንት (ሐሙስ) ቢያደንቁም “የፍልስጥዔማዊያን መፈናቀል ግን ቀይ መሥመር ነው” ብለዋል።

ብዙ ጊዜ በተፋላሚ ወገኖቹ መካከል አደራዳሪ እየሆነች የምትላከው ግብፅ ግጭቱ ከተጫረበት ካለፈው መስከረም 26 አንስቶ ተኩሱ እንዲቆም ስትጥር ቆይታለች።

ኤል-ሲሲ ካይሮ ውስጥ በሺሆች የሚቆጠሩ በተሣተፉበት የፍልስጥዔማዊያን ጉባዔ ፊት ሲናገሩ “ከዩናይትድ ስቴትስና ከካታር ወንድሞቻችን ጋር ሆነን ያደረግናቸው ጥረቶች ተኩስ ለሰብዓዊ ጉዳዮች ሲባል እንዲቆም ያስቻለውን ስምምነት አጎናፅፈዋል” ብለዋል።

የፍልስጥዔም ስደተኞች ወደ ግብፅ ምድር የመጉረፋቸውን ሃሳብ ጨርሶ እንደማይቀበሉ ኤል-ሲሲ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

"መፈናቀል ቀይ መሥመር ነው፤ አንቀበለውም፣ እንዲሆንም አንፈቅድም" ብለዋል ፕሬዚዳንት ሲሲ።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም “ፍልስጥዔማዊያን ወደ ግብፅ ምድር መውጣታቸው የፍልስጥዔም የግዛት ጥያቄን ውድቅ ያደርገዋል፤ የግብፅን ደኅንነትና ኢኮኖሚም አደጋ ላይ ይጥላል ብላ ግብፅ ትፈራለች” ብለዋል።

ይሁን እንጂ ግብፅ ባለፉት ሣምንታት በሺሆች የሚቆጠሩ ድርብ ዜግነት ያላቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ የተጎዱና የታመሙ ፍልስጥዔማዊያን ከጋዛ በራፋ ኬላ በኩል እንዲገቡ ፈቅዳለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG