በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብጹ ፕሬዝደንት ቻይናን እየጎበኙ ነው


የቻይና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ፣ የግብጹ ፕሬዝደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ
የቻይና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ፣ የግብጹ ፕሬዝደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ

የግብጹ ፕሬዝደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ዛሬ ረቡዕ ቻይና በመግባት ከሃገሪቱ ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ጋራ ተገናኝተዋል።

ቤጂንግ በዚህ ሣምንት የዓረብ ሃገራት መሪዎችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ነች፡፡ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት ላይ “የጋራ ድምፅ” በሚል የገለጹትን ለመፍጠርና ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ያለመ ስብሰባ መሆኑ ተነግሯል።
ሁለቱ መሪዎች በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች እንዲሁም በሁለቱ ሃገራት መካከል በበርካታ መስኮች የቅርብ ግንኙነት በመፍጠር ላይ እንደሚወያዩ የግብጹ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት አስታውቋል።

ቤጂንግ ከዓረቡ ዓለም ጋራ የቅርብ ግንኙነት ለመፍጠር በመጣር ላይ ስትሆን፣ ባለፈው ዓመት በኢራን እና በባላንጣዋ ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲሻሻል ሽምግልና ገብታለች፡፡

መካከለኛው መሥራቅን በተመለከተም ለፍልስጤማውያን ዓላማዎችና የሁለት ሃገራት መፍትሄ ያላትን ድጋፍ ገልጻለች፡፡ ባለፈው ወርም የፍልስጤማውያን ቡድን የሆኑትን ሐማስ እና ፋታህ ጥልቅ ውይይት እንዲያደርጉ አስተናግዳለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG