በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብጽ ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሆሳም ባጋትን ነፃ ለቀቀች


የግብጽ የጦር ሰራዊት ያሰረውን ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሆሳም ባጋትን በዛሬው ዕለት ለቆታል።

የግብጽ የጦር ሰራዊት ያሰረውን ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሆሳም ባጋትን፣ መንግስቱ በዛሬው ዕለት ነፃ ለቆታል።

ጋዜጠኛው የተለቀቀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ኣንድ የሰባዓዊ መብት ተሙዋጋች ቡድን እስሩን ባወገዙት በማግስቱ መሆኑ ታውቋል።

የግብጽ ባለስልጣናት ባጋትን ዕሁድ ዕለት ያሰሩት ሃያ ስድስት መኮንኖች መንግስት ልትገለብጡ ኣሲራችዋል ተብለው በጦር ፍርድ ቤት ተበይኖባቸዋል ብሎ ባለፈው ወር ባቀረበው ዘገባ የሃሰት ወሬ ኣሰራጭተሃል በማለት ወንጅለውት ነው።

ባጋትን እጅግ ታዋቂ ከሆኑ የግብጽ የሰብዓዊ መብት ተሙዋጋቾች ኣንዱ ሲሆን የግብጽ መብቶች ተሙዋጋች ድርጅት የተባለው ቡድን መስራችም ነው።

ጋዜጠኛው ጦር ፍርድ ቤት መቅረብ ይኖርበት እንደሆን ለጊዜው ኣናውቅም ብለዋል ጠበቃው። ጦር ሰራዊቱ ባጋትን የሀገር ብሔራዊ ደህንነት የሚጎዳ ተግባር ፈጽሙዋል፡ ሳይፈቀድለት ስለጦር ሃይሉ ጽሁፍ ኣውጥቷል ሲል ወንጅሎታል።

XS
SM
MD
LG