በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፅ ድንበሯን ለመጠበቅ ሁሉንም እምርጃዎች እንደምትወስድ አስታወቀች


የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ
የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ

ግብፅ ድንበሯን ለመጠበቅ “ሁሉንም እርምጃዎች” ትወስዳለች ሲሉ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ ትናንት ማክሰኞ ለአገሪቱ ምክር ቤት ተናግረዋል፡፡

“ግብፅ የድንበሮቿን ጥበቃ የሚያረጋግጡ እርምጃዎችን ከመውሰድ ወደ ኋላ አትልም”ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ሰርጥ ወደ ግዛቷ ለማስገባት የሚደረገውን ማንኛውንም ሙከራ እንደማትቀበለው ተናግረዋል፡፡

የእስራኤልና ሐማስ ግጭት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ግብፅ ተፈናቃይ ፍልስጤማውያንን ተቀባይ አገር እንደማትሆን ያለማቋረጥ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

የሰሜን አፍሪካዊቷ አገር፣ የፍልስጤማውያን ጋዛን ለቀው ወደ ግብፅ ምድር መውጣት፣ የፍልስጤምን የግዛት ጥያቄ ውድቅ ሊያደርገውና የግብፅን ደህንነት እና ኢኮኖሚም አደጋ ላይ ይጥላል የሚል ትልቅ ስጋት እንዳላት ተመልክቷል፡፡

ይህም ሆኖ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥምር ዜግነት ያላቸው ሰዎች እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ቁስለኛ እና ህሙማን ፍልስጤማውያን ባላፉት ሳምንታት ከጋዛ ወደ ግብፅ አቋርጠው መግባታቸው ተጠቅሷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG