በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስት ግብጻውያን መነኩሴዎች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተገደሉ


በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ ገዳም ውስጥ ሦስት ግብጻዊያን የኮፕቲክ መነኩሴዎች መገደላቸውን በግብጽ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ትናንት አስታውቋል።

የደቡብ አፍሩካ ፖሊስ በበኩሉ፣ በግድያው የተጠረጠረን አንድ የ 35 ዓመት ግለሰብ ዛሬ መያዙን አስታውቋል። ግለሰቡ ነገ ሐሙስ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብም ታውቋል።

“በገዳማችን ውስጥ ሦስት መነኩሴዎች የወንጀል ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል” ሲሉ የቤተክርስቲያኑ ቃል አቀባይ በማኅበራዊ ሚዲያ አስታውቀዋል። ቃል አቀባዩ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።

የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን ፕሪቶሪያ ከሚገኘው ኤምባሲው ጋራ በመሆን በቅርብ እየተከታተለው መሆኑን አስታውቋል።

በፕሪቶሪያ አቅራቢያ በምትገኘው ኩሊናን በተሰኘች ከተማ ባለ የኮፕቲክ ገዳም ሶሶት ቄሶች የመገደላቸውን ጉዳይ ባለሥልጣናት በመመርመር ላይ መሆናቸውን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ቃል አቀባይ አስታውቋል።

ሟቾቹ በስለት ተወግተው መገኘታቸውን እና አንድ ከጥቃቱ ያመለጡ መነኩሴ ደግሞ በብረት ዱላ መመታቸውን እንዳስታወቁ ቃል አቀባዩ ጨምረው ገልጸዋል።

የጥቃቱ ምክንያት እስከአ አሁን አለመታወቁን እና ጥቃት አድራሾቹ ዋጋ ያላቸውን ንብረቶችን ይዘው እንዳልሄዱ ቃል አቀባዩ ማስታወቃቸውን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG