በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኅዳሴ ግድብ የአምስት የአረብ መሪዎች ስብሰባ አጀንዳ ይሆናል


የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታ አል-ሲሲ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ቢን ዛይድ ከካይሮ በስተ ሰሜን-ምዕራብ ሜዲቴራኔያን ባህር ጠርዝ ላይ በምትገኘው ኤል-አለሜይን ከተማ አቀባበል ሲያደርጉላቸው።
የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታ አል-ሲሲ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ቢን ዛይድ ከካይሮ በስተ ሰሜን-ምዕራብ ሜዲቴራኔያን ባህር ጠርዝ ላይ በምትገኘው ኤል-አለሜይን ከተማ አቀባበል ሲያደርጉላቸው።

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ የአምስት አረብ ሃገሮችን ስብሰባ እያስተናገዱ መሆናቸውን ከመንግሥታቸው የወጣውን መግለጫ ጠቅሶ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ከካይሮ ዘግቧል።

የዩክሬንን ጦርነት ተከትሎ የተፈጠረው የኃይልና የምግብ አቅርቦት ቀውስ ከስብሰባው አጀንዳዎች አንዱ እንደሆነ ተገልጿል።

ግብፅና ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ የገቡበት የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ለውይይት እንደሚቀርብ የመንግሥቱ ዕለታዊ ጋዜጣ አል-አህራም ዲፕሎማሲያዊ ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡን ኤኤፍፒ በሪፖርቱ ጠቁሞ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው የ4.2 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ነዋይ ግዙፍ ግድብ መሠረቱ ከአሥር ዓመት በፊት ሲጣል ጀምሮ የጭቅጭቅ መንስዔ ሆኖ መቆየቱን አመልክቷል።

ከካይሮ በስተ ሰሜን-ምዕራብ ሜዲቴራኔያን ባህር ጠርዝ ላይ በምትገኘው ኤል-አለሜይን ከተማ የተሰባሰቡት የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታ አል-ሲሲ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ቢን ዛይድ፣ የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጣፋ አል-ካዴሚ፣ የዮርዳኖስ ንጉሥ ዳግማዊ አብደላና የባህሬን ንጉሥ ሃማድ መሆናቸው ታውቋል።

አምስቱ መሪዎች ትናንት፤ ሰኞ ተገናኝተው በጋራ ግንኙነቶቻቸውና ትብብራቸውን መጠናከር ላይ ሃሳብ መቀያየራቸውንና ስብሰባው ዛሬ በይፋ መጀመሩን የዜና ወኪሉ ዘግቧል።

የመን፣ ሶሪያና ሊቢያ ውስጥ የሚካሄዱት ጦርነቶች፣ እንዲሁም በፍልስጥዔምና በእሥራኤል መካከል ያሉ ግጭቶች የስብሰባው አጀንዳ ይሆናሉ ተብሏል።

ከስብሰባው ተሣታፊዎች ለእሥራኤል ዕውቅና ያልሰጠች ብቸኛዋ ሀገር ኢራቅ ስትሆን ግብፅ እአአ በ1979፤ ዮርዳኖስ እአአ በ1994 ከእሥራኤል ጋር ሰላም ፈጥረዋል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ባህሬን ደግሞ ከእሥራኤል ጋር መደበኛ ግንኙነት የጀመሩት ከሃያ ዓመት በፊት ነበር።

XS
SM
MD
LG