በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሞርሲ ፍርድ ተቀለበሰ


የቀድሞ የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሞርሲ
የቀድሞ የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሞርሲ

በቀድሞ የግብጽ ፕሬዚዳንት በሙሀመድ ሞርሲ ላይ ተወስኖባቸው የነበረውን የዕድሜ ይፍታህ ፍርድ የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ቀልብሶታል።

ሠበር ሰሚው ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት የቀድሞው መሪ በሌላ ክስ ተላልፎባቸው የነበረውን የሞት ፍርድ ሰርዞ ክሱ እንደገና እንዲታይ ወስኗል።

የግብፁ ከፍተኛ ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት ዛሬ የቀለበሰው ከሁለቱ የዕድሜ ይፍታህ ፍርዶች አንዱን ሲሆን ከፍሊስጤሙ ሃማስ ቡድን ጋር በተያያዘ የስላላ ወንጀል ክስ የተበየነባቸውን ነው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የሞርሲ ፍርድ ተቀለበሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:55 0:00

XS
SM
MD
LG