በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን ክስ ግብፅ እንደምትደግፍ አስታወቀች


የእስራኤል የቦምብ ጥቃት ተከትሎ በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ በጃባሊያ ጭስ ይታያል፤ ሰሜን ጋዛ ሰርጥ እአአ ግንቦት 12/2024
የእስራኤል የቦምብ ጥቃት ተከትሎ በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ በጃባሊያ ጭስ ይታያል፤ ሰሜን ጋዛ ሰርጥ እአአ ግንቦት 12/2024

እስራኤል ከሐማስ ጋራ በምታደርገው ጦርነት የዘር ማጥፋት ፈፅማለች በሚል ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፍ የፍትህ ችሎት ያቀረበችውን ክስ ግብፅ እንደምትደግፍ ትላንት እሁድ አስታውቃለች፡፡

እስራኤል በጋዛ የምታካሄደውን ወታደራዊ ዘመቻ እንድስታስቆም ትዕዛዝ እንዲሰጥ ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ባለፈው ታህሳስ ክስ ከፍታለች፡፡

“እስራኤል የጀኖሳይድ ስምምነት መጣሷን በመቀጠል ለዓለም አቀፍ ሕግጋት ያላትን ንቀት በማሳየት ላይ ነች” ስትል ደቡብ አፍሪካ ባለፈው ዓርብ በድጋሚ ክሷን አሰምታለች፡፡

እስራኤል ስልታዊ በሆነ መንገድ ሲቪሎችን ዒላማ በማድረጓ እና መሠረተ ለማቶችን በማውደሟ እንዲሁም ፍልስጤማውያንን በማፈናቀሏ”

ግብፅ ትላንት እሁድ ክሱን ለመደገፍ የወሰነችው “እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በፍልስጤማውያን ሲቪሎች ላይ በማድረስ ላይ ያለችው ጥቃት የከፋ በመሆኑ” እንደሆነ አስታውቃለች፡፡

ግብፅ በተጨማሪም “እስራኤል ስልታዊ በሆነ መንገድ ሲቪሎችን ዒላማ በማድረጓ እና መሠረተ ለማቶችን በማውደሟ እንዲሁም ፍልስጤማውያንን በማፈናቀሏ” ምክንያት ክሱን እንደደገፈች አስታውቃለች፡፡

ሐማስ ትላንት ምሽቱን ባወጣው መግለጫ የግብፅን አቋም አድንቆ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ሃገራት ፍልስጤማውያንን በመደገፍ ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG