በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብጽ ሰባት ሺሕ የሚሆኑ የውጭ ዜጎችን ከጋዛ ለማስወጣት እንደምትተባበር ገለጸች


ጥምር ዜግነት ያላቸው ፍልስጤማውያን ወደ ግብፅ ለመሻገር ሲመዘገቡ፤ እአአ ህዳር 2/2023
ጥምር ዜግነት ያላቸው ፍልስጤማውያን ወደ ግብፅ ለመሻገር ሲመዘገቡ፤ እአአ ህዳር 2/2023

ሰባት ሺሕ የሚደርሱ የውጭ ዜጎችንና ጥምር ዜግነት ያላቸውን ጋዛውያን በማስወጣት እንደምትተባበር ግብጽ አስታውቃለች፡፡

የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ 400 የሚኾኑት፣ ዛሬ ኀሙስ፣ የራፋን ደንበር አቋርጠው ይወጣሉ። የመጀመሪያዎቹ ተጓዦች፣ ዛሬ ዐርብ ግብጽ መድረስ እንደጀመሩ፣ ባለሥልጣናት ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ፣ በግብጽ እና በጋዛ መሀከል ያለው የራፋ መተላለፊያ፣ ትላንት ረቡዕ እንደተከፈተ ይታወሳል።

የግብጽ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስማኤል ካሂራት፣ ለዲፕሎማቶች በሰጡት መግለጫ፣ የ60 ሀገራት ዜጎችን ከጋዛ የማስወጣቱንና የመቀበሉን ሥራ፣ አገራቸው እንደምትራዳ አስታውቀዋል።

በጋዛ በኩል የመተላለፊያው ሓላፊ ሂሻም አድዋን እንዳሉት፣ አንድ መቶ የሚኾኑ ጉዳተኞች እና አሜሪካውያንን ጨምሮ፣ 400 የውጭ ሀገራት ዜጎች፣ ዛሬ ኀሙስ በራፋ ይሻገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ትላንት ረቡዕ፣ 361 የውጭ ዜጎች ወደ ግብጽ እንደገቡ፣ ባለሥልጣኑ ተናግረዋል። እነዚኽም፥ የኦስትሪያ፣ የጣሊያን፣ የፈረንሳይ እና የጀርመን ዜጎች እንደሚገኙበት፣ የሀገራቱ መንግሥታት አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG