ግብጽ የበአባይ ተፋሰስ ሀገሮች የወንዙን ውሀ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ባደረጉት የመሰረተ-ሃሳብ ስምምነት ለመደራደር እንድትችል ስምምነቱን የማጽደቁ ጉዳይ አዲስ የግብጽ መንግስት እስከሚመሰረትበት ጊዜ ድረስ ለማዘግየት ኢትዮጵያ ተስማምታለች።
“ኢትዮጵያ የወቅቱን የግብጽ ሁኔታ ስለምታጤን የራሳቸውን መንግስት መስርተው ፕረዚዳንታቸውን በዲሞክራስያዊ ሂደት እስከሚመርጡበት ጊዜ ድረስ ለግብጽ ጊዜ መስጠቱ ብልህነትና አሰተዋይነት አድርጋ ታየዋለች።" ብልለዋ በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር መሐሙድ ዲሪር ጌዲ።
የግብጽ ልዑካን መሪ ሙስጣፋ ኤል-ጊንዲ ደግሞ “የሰላሳ አመታት የሙባረክ አገዛዝ ግብጻውይን እርሶን እንዳያምኑ አድርጓል። ውህውን በማቆም ሊገድሏቸው የተነሱ ሆኖ ይሰማቸዋል ብየ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገርዃቸው።” በማለት አስረድተዋል።