በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፃውያን ለሁለተኛ ቀን ድምፅ ሲሰጡ ውለዋል


ግብፃውያ ትናንት እሁድ ድምፅ ሲሰጡ ውለዋል
ግብፃውያ ትናንት እሁድ ድምፅ ሲሰጡ ውለዋል

ፕሬዝደንታቸውን ለመምረጥ ትናንት እሁድ ድምፅ መስጠት የጀመሩት ግብፃውያን፣ ዛሬ ሰኞም ለሁለተኛ ቀን ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል።

በምርጫው፤ በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ካለምንም ተፎካካሪ እንደሚያሸንፉ እና እ.አ.አ እስከ 2030፣ ማለትም ለሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት በሥልጣን ላይ እንደሚቆዩ ይጠበቃል።

ለሶስት ቀናት ያህል ድምፅ የሚሰጥበት ምርጫ በመካሄድ ላይ ያለው፣ አገሪቱ በታሪኳ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ በተመታችበት ወቅት እና 105 ሚሊዮን ከሚሆነው ሕዝብ ውስጥ፣ ከሶስት እጅ ሁለቱ ከድህነት ወለል በታች በሚኖርበት ወቅት ነው።

የኢኮኖሚ ቀውሱ የመጣው በብልሹ አስተዳደር፣ እንዲሁም ኮቪድ 19 ባስከተለው ዳፋ እና በዩክሬን የሚካሄደው ጦርነት በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ባስከተለው ችግር ነው።

ምርጫው በተጨማሪም በእስራኤል እና ሐማስ መካከል የሚካሄደው ጦርነት ጥላውን አጥልቶበታል ተብሏል።

የግብፃውያኑ ትኩረት፣ በአጠቃላይ በሚባል ሁኔታ፣ በምሥራቅ የአገሪቱ ድንበር በኩል ያለው ጦርነት እና የፍልስጤማውያን ስቃይ ላይ ነው ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG