በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አምነስቲ ግብፅ በርካታ ኤርትራዊያንን ስደተኞችን ከሃገር ታባርራለች አለ


ግብፅ ወደ ሃገራቸው ቢመለሱ ሊደርስባቸው የሚችለውን አደገኛ ጉዳት ችላ በማለትና ባለፉት ሁለት ሳምንታት ዓለም አቀፉን ህግ በመጣስ በግብፅ የፖለቲካ ጥገኝነት (አሳይለም) የጠየቁ 31 ኤርትራውያንን ከአገር አባራለች ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወቀሰ፡፡

መሰረቱን በለንደን ያደረገው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ግብፅ እስካሁን ወደ 50 የሚደርሱ ኤርትራዊያን ስደተኞች በማሰር ወደ አገራቸው ለማባረር በዝግጅት ላይ መሆኗን አስታውቋል፡፡

ይህ ወደ ኤርትራ መልሶ የማባረሩ እርምጃ እየጨመረ መምጣቱ አሳስቢ በመሆኑ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ሲም አምነስቲ አሳስቧል።

የአምነስቲ ተወካይ ፊሊፕ ሉተር “ስደተኞቹ በዘፈቀደ እየተያዙ የግዳጅ ምርመራ እየተካሄደባቸውና ስቃይ እየደረሰባቸው ስለመሆኑ በቂ መረጃ አለ” በማለት የተናገሩ ሲሆን “ይህ ከሃገር የማባረር እርምጃ ግብፅ የገባቸውን ዓለም አቀፍ ግዴታ የጣሰችበት ስለሆነ በአስቸኳይ መቆም አለበት” ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽነር እስካለፈው ዓመት ድረስ በግብፅ 21ሺ ኤርትራውያን ስደተኞች መመዝገቡን አስታውቋል፡

ይሁን እንጂ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ኤርትራውያን ቁጥር ከዚያ በላይ ነው ይላል፡፡ ምክንያቱም በግብፅ ያሉ ብዙዎቹ ኤርትራውያን ወደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንዳይሄዱ ይከለከላሉ ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG