በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በራፋ ተፈናቃዮች ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ግብፅ አወገዘች


 የእስራኤል ጥቃት ተከትሎ ራፋ ውስጥ የተፈናቃዮች ድንኳን ወድሞ ይታያል፤ ደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ
የእስራኤል ጥቃት ተከትሎ ራፋ ውስጥ የተፈናቃዮች ድንኳን ወድሞ ይታያል፤ ደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ

የእስራኤል ኃይሎች “ሆን ብለው በራፋ በድንኳን ውስጥ በሚኖሩ ተፈናቃዮች ላይ ድብደባ ፈፅመዋል” ስትል ግብፅ ጥቃቱን አውግዛለች፡፡ በጥቃቱ ቢያንስ 40 ሰዎች መገደላቸውን በጋዛ የሚገኙ የሲቪል ድርጅቶች አስታውቀዋል።

የግብፅ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ወታደራዊ ዘመቻዎች በአፋጣኝ እንዲቆሙ ሲል ዓለም አቀፉ የወንጅል ችሎት የሰጠውን ትዕዛዝ እስራኤል እንድታከብር ጠይቋል።

“ጥቃቱ ግልፅ የሆነ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግጋት ጥሰት ነው” ያለው ሚኒስቴሩ “እራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሲቪሎችን በማጥቃትና በጋዛ ሆን ብሎ ዕልቂትና ውድመት በመፍጠር ስፍራው ወደፊት መኖሪያ እንዳይሆን ያለመ ፖሊሲ ነው” ሲል አውግዟል።

ዮርዳኖስም በበኩሏ ጥቃቱን በማውገዝ፣ “ተከታታይ የጦር ወንጀሎችን በመፈጸም ላይ ነች” ስትል እስራኤልን ከሳለች፡፡

ጥቃቱ የዓለም አቀፉን የወጀል ችሎት ትዕዛዝ እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግጋትን የጣሰ መሆኑንም ዮርዳኖስ አመልክታለች፡፡

በተፈናቃዮች መጠለያ ላይ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል ሲሉ የፍልስጤማውያን ፕሬዝደንት ቢሮ እና ሐማስ አስታውቀዋል።

እስራኤል በበኩሏ፣ በአየር በፈጸመችው ጥቃት ሁለት የሐማስ መሪዎችን መግደሏን እና ሲቪሎች ተገድለዋል የሚሉትን ሪፕርቶች እየመረመረች መሆኑን አስታውቃለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG