በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካይሮ የፀጥታ ቀውስ ውስጥ ገባች


Mideast Egypt
Mideast Egypt

ዋይት ሃውስ የኃይል እርምጃውን አወገዘ።





የዩናይትድ ስቴትስን ተቃውሞ ያሰሙት የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የፕሬስ ኃላፊ ጆሽ ኤርነስት፤ ረቡዕ - ነሐሴ 8/2005 ዓ.ም፣ ዋይት ሃውስ
የዩናይትድ ስቴትስን ተቃውሞ ያሰሙት የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የፕሬስ ኃላፊ ጆሽ ኤርነስት፤ ረቡዕ - ነሐሴ 8/2005 ዓ.ም፣ ዋይት ሃውስ

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:35 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በዛሬው የኃይል እርምጃ የተገደሉ ግብፃዊያን አስከሬኖች
በዛሬው የኃይል እርምጃ የተገደሉ ግብፃዊያን አስከሬኖች
በግብፅ መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በዋና ከተማይቱ ካይሮ ተቃዋሚዎች የተሰባሰቡባቸውን የድንኳን ካምፖች ወርረው ጥቃት አድርሰዋል።
በግጭቱ ስለሞቱና ስለቆሰሉ ሰዎች ከሁለቱም ወገኖች በኩል አንዱ ከሌላው የሚጣረስ አኀዝ እየተሰጠ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ መወሰዱን በብርቱ እንደምታወግዝ ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች፡፡

“በአመፁና በሁከቱ ለተገደሉና ለተጎዱ ቤተሰቦች ሁሉ ኀዘናችንን እንገልፃለን” ብሏል ይኸው ዛሬ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት የወጣው መግለጫ፡፡

“የግብፅ ጦርና የፀጥታ ኃይሎቹ ትዕግሥት እንዲያሣዩ ደጋግመን ጠይቀናል” የሚለው የዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት መግለጫ መንግሥቱ የዜጎቹን አጠቃላይ መብቶች እንዲያከብር ዩናይትድ ስቴትስ እንደምታሳስብ አስታውቋል፡፡

ሰልፈኞቹም ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲገልፁ ጠይቋል ዋይት ሃውስ፡፡

መግለጫው አክሎም “ኃይል የሚያመጣው ነገር ቢኖር ግብፅ ወደ ዘላቂ መረጋጋትና ዴሞክራሲ እንዳታመራ የሚያደርገውን ችግር ይበልጥ ማባባስ ብቻ ከመሆኑም በላይ ጊዜያዊው መንግሥት በዕርቅ ጎዳና ለመግፋት ከገባው ቃል ጋር ይጋጫል” ብሏል፡፡

ወደ አስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ የመመለስን ሃሣብ ዩናይትድ ስቴትስ በብርቱ እንደምትቃወም ዋይት ሃውስ አመልክቶ በሰላም የመሰብሰብን ነፃነትና የሕግን አግባብነት ያለው አካሄድ ጨምሮ መንግሥቱ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብር አሳስቧል፡፡

“ካይሮ ላይ ምን እየተደረገ እንዳለ ዓለም እየታዘበ ነው - ያለው የዋይት ሃውስ መግለጫ - የግብፅ መንግሥትና ሁሉም ግብፅ ውስጥ ያሉ ወገኖች ከአመፅ እንዲቆጠቡና ልዩነቶቻቸውን በሰላም እንዲፈቱ እናሳስባለን፡፡” ሲል ደምድሟል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የግብፅ ወታደራዊ ኃይል ሰላማዊ ሰልፍ ባካሄዱ በቀድሞው ፕሬዚደንት ሞሐመድ ሞርሲ ደጋፊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ በመላው ዓለም ከሚገኙና እስላማዊውን መሪ ከሚደግፉ መንግሥታት ብርቱ ተቃውሞና ውግዘት ደረሶበታል፤ አመፁ እንዲገታም ጥሪ ቀርቧል።

የአውሮፓ ኃያላን ባስተላለፉት መልዕክት በወታደር የሚደገፈው ጊዜያዊ መንግሥትም ሆነ እሥላማዊው ተቃዋሚ ወገን አመፅ አቁመው ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

የቱርኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ራሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ዛሬ ረቡዕ ካይሮ ውስጥ የተፈፀመውን ግድያ «ጭፍጨፋ» ብለው የጠሩት ሲሆን የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤትና የአረብ ማኅበር ጣልቃ በመግባት አመፁን እንዲያስቆሙ አሳስበዋል።

ቱርክ፣ የሞሐመድ ሞርሲን ከሥልጣን መወገድ በብርቱ ከሚቃወሙ አገሮቸ አንዷ መሆኗ ይታወቃል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ-ሙንም አመፁን በብርቱ እንደሚያወግዙ አመልክተው የግብፅ ባለሥልጣናት በአመዛኙ ሙስሊም በሆኑ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱትን የኃይል እርምጃ እንደሚያወግዙ ማስታወቃቸውን ቃል አቀባያቸው ተናግረዋል፡፡

ኢራንም ተቃዋሚዎቹን ለመበተን የተወሰደውን የኃይል እርምጃ እንደ ቱርክ ሁሉ “ጭፍጨፋ” ብላ ጠርታዋለች፡፡

የሚስተር ሞርሲ እሥላማዊ ወንድማማችነት ንቅናቄ የጋፊ የሆነችው ካታርም እንዲሁ የፀጥታ ኃይሎቹን የኃይል እርምጃ አውግዛለች፡፡

“ከካይሮ የሚሰማው ወሬ እጅግ የሚያስጨንቅ ነው” ያሉት የአውሮፓ ሕብረቱ ቃልአቀባይ ፒተር ስታኖ አመፃ ወደ መፍትሔ እንደማይወስድ አሳስበው ሁሉም ወገኖች መቻል እንዲኖራቸው ጠይቀዋል፡፡

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊልያም ሄግም የግብፅ መንግሥት ተቃዋሚዎቹን ለመበተን የወሰደውን እርምጃ በብርቱ እንደሚያወግዙ ገልፀው በሁለቱም ወገን ያሉ መሪዎች አመፁ እንዳይቀጥል እንዲሠሩ ጠይቀዋል፡፡
XS
SM
MD
LG