በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብጽ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ዋጋ ያላቸውን የመንግሥት ድርጅቶች ልትሸጥ ነው


ካይሮ፣ ግብፅ
ካይሮ፣ ግብፅ

የተዳከመውን የአገሪቱን የግል ዘርፍ ለማበረታታት በሚል፣ ግብጽ፥ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ዋጋ ያላቸውን የመንግሥት ድርጅቶችን ለመሸጥ፣ በርካታ ስምምነቶችን እንደፈጸመች አስታወቀች፡፡

የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ፣ በቴሌቭዥን በተላለፈ ጋዜጣዊ መግለጫቸው እንደተናገሩት፣ እስከ አሁን ከተፈጸመው የድርጅቶቹ ሽያጭ፣ መንግሥት፥ 1ነጥብ9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል።

በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደረው ‘ቴሌኮም ኢጂፕት’ ድርሻ ተሽጦ፣ 1.9 ቢሊዮን ዶላር እንድተገኘ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀው፣ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ከመናገር ተቆጥበዋል።

እስከ 30 በመቶ የሚኾነው የአገሪቱ ፔትሮሊየም ኩባንያ፣ አቡዳቢ ለሚገኝ ኩባንያ ተሽጦ፣ 800 ሚሊዮን ዶላር እንደተገኘም ታውቋል።

የተንኮታኮተው የግብጽ ኢኮኖሚ እንዲያገግም፣ አገሪቱ፥ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF)፣ ሦስት ቢሊዮን ዶላር የዋስትና ጥቅል እንደምታገኝ ቃል የተገባላት ሲኾን፣ የመንግሥት ድርጅቶቹን ድርሻ የመሸጡ ፕሮግራም፣ የዚኹ ሒደት አካል እንደኾነ ታውቋል።

በመንግሥት የተያዙ ተቋማትን ለመቀነስ እና ወደ ግል ለማዛወር በተያዘው ዕቅድ፣ ግብጽ፥ 32 የመንግሥት ድርጅቶችን ድርሻ ለመሸጥ ዐቅዳለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG