በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትውልድ የሚቀርፀው የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቭዥን


የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቭዥን ጣቢያ
የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቭዥን ጣቢያ

በኮሮና ቀውስ ወቅት ትምህርት ቤቶች፣ መዋእለ ሕፃናት እና ሌሎች የልጆች መጫወቻና መዋያ ቦታዎች በመዘጋታቸው ልጆች ሙሉ ጊዜያቸውን ቤት ለመዋል ተገደዋል። በዚህ የቤት ቆይታ ወቅት ልጆች በቴሌቭዥንና በሌሎች የኤሌክትሮኒስ ሚዲያዎች ላይ የሚያጠፉት ግዜ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ጥናቶች ያመለክታሉ።

ለምሳሌ በአሜሪካን ሃገር የተደረገ ጥናት ልጆች ቤት በመዋላቸው ምክንያት የቀን ቴሌቭዥን ተመልካቾች ቁጥር 40ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በዚህ መጠን ጊዜያቸውን ቴሌቭዥን ላይ የሚያጠፉ ሕፃናትና ልጆች ለዕድሜያቸው ተመጣጣኝ የሆኑ ፕሮግራሞችን እንዲያዩና በሥነ-ምግባር የሚያንፁ ገንቢ ትምህርቶችን እንዲያገኙ በማገዝ “የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን” የተሰኘው፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የሕፃናት የቴሌቭዥን ጣቢያ ትልቅ አስተዋፅዖ እያደረገ ነው።

በአስተማሪነቱ የወላጆችን አድናቆት ያተረፈውን የዚህን የቴሌቭዥን ጣቢያ የአንድ ዓመት የስኬት ጉዞ አስመልክቶ የጣቢያውን መስራች ቢኒያም ከበደን አነጋግረናል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ትውልድ የሚቀርፀው የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቭዥን
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:29 0:00


XS
SM
MD
LG