በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል ከ185ሺሕ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተናን አይወስዱም


ፎቶ ፋይል፦ ባህር ዳር ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ ባህር ዳር ከተማ

በአማራ ክልል በቀጠለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት፣ ዛሬ ማክሰኞ፣ በተጀመረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መቀመጥ የነበረባቸው ከ185 ሺሕ በላይ ተማሪዎች፣ ፈተናውን አለመውሰዳቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በአማራ ክልል ከ185ሺሕ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተናን አይወስዱም
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:02 0:00

የትምህርት ቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ ግጭቱ ባለባቸው የምዕራብ፣ ምሥራቅ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች ያሉ ተማሪዎች፣ ዓመቱን በሙሉ ያልተማሩና ጀምረው ያቋረጡ በመኾናቸው ለፈተናው አይቀመጡም።

እስከ ቀጣዩ ዓመት መስከረም ወር ድረስ ማካካሻ ተሰጥቷቸው ፈተናውን እንዲወስዱ ጥረት እየተደረገ መኾኑንም አቶ ጌታቸው አክለው ገልጸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG