በያመቱ በዚህ ዕለት፥ የሕዳር ወር በገባ አራተኛው ሃሙስ ቤተሰቦች ተሰባስበው፤ የሕይወትን ትሩፋቶች፤ ጸጋና በረከቶች በማወደስ ምሥጋና በማቅረብ የሚያከብሩት ብሔራዊ ክብረ-በዓል ነው።
ክብረ-በዓሉ ዘመን የጠገበ መሆኑን በማስታወስ የተንደረደረው የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ፤ ከመጀመሪያዎቹ እንግሊዛውያን ሠፋሪዎች አንዳንዶቹ ወዲህ ወደ ሰሜን አሜሪካ ከገቡበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1620ዎቹ እምብዛም ለሰዎች መኖሪያ በማያመቸው ጫካና እጅግ የከፉ የክረምት ወራት አሳልፈው የመጀመሪያውን ያማረ የሰብል ምርት መሰብሰብ መቻላቸውን ተከትሎ የገጠማቸውን መልካም ዕድል ለማወደስ ፋታ ከወሰዱበት ጊዜ አንስቶ መከበር መጀመሩን ይጠቁማል።