በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምዕራብ አፍሪቃ የምጣኔ ሃብት ማኅበረሰብ በማሊና ቡርኪናፋሶ ላይ ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ አነሳ


የምዕራብ አፍሪቃ ነጻ የንግድ ቀጣና - ኢኮዋስ አባል አገራት መሪዎች፤ ጋና ዋና አክራ ላይ ያደረጉት ስብሰባ
የምዕራብ አፍሪቃ ነጻ የንግድ ቀጣና - ኢኮዋስ አባል አገራት መሪዎች፤ ጋና ዋና አክራ ላይ ያደረጉት ስብሰባ

የምዕራብ አፍሪቃ ነጻ የንግድ ቀጣና - ኢኮዋስ አባል አገራት መሪዎች የማሊ ወታደራዊ መሪዎች በመጭው 24 ወራት ውስጥ በዚያች አገር ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ለማምጣት ያቀረቡትን ዕቅድ እና አዲስ የምርጫ ሕግ ማውጣታቸውን ተከትሎ ነው፣ በማሊ ላይ ካሁን ቀደም ጥለውት የነበረውን ማዕቀብ ያነሱት፡፡

ማሊ የኢኮዋስ ጠንካራ ማዕቀብ የተጣለባት ወታደራዊ ጁንታው ቀደም ሲል ይፋ የተደረገውን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ዕቅድ አልከተል ካለ በኋላ ነው፡፡ ማዕቀቡን ተከትሎም ማሊ ያለባትን በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚሰላ ዕዳ መክፈል እንደተሳናት ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ጋና ዋና ከተማይቱ አክራ ላይ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ ጁንታ መሪዎች በ24 ወራት ጊዜ ውስጥ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ቃል

በመግባታቸው በዚያች አገር ላይ ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ መነሳቱ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG