የኢትዮጵያ መንግሥት በተጠናቀቀው ዓመት መጨረሻ ላይ የምጣኔ ሃብት ማሻሻያ ፖሊሲውን ይፋ አድርጓል፡፡ ከማሻሻያው ጋራ ተያይዞም፣ የውጭ ምንዛሪ ተመኑ ገበያ መር እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በዚህ መነሻነት፣ ‘የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ይዞታ በአዲሱ አመት ምን መልክ ይኖረዋል’ ሲል የአሜሪካ ድምፅ የጠየቃቸው ባለሙያዎች፣ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ ባለሙያዎቹ፣ መንግሥት ባደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተስማምተው፣ 2017 ዓ.ም የማሻሻያ ፖሊሲው የሚፈተንበት ዓመት ይሆናል ይላሉ፡፡
ማሻሻያው ውጤት እንዲያመጣ፣ ከሁሉም በላይ ሰላምና መረጋጋት ያስፈልጋል የሚሉት ባለሙያዎቹ፣ አሁን በሀገሪቱ ያለው ግጭት እና ጦርነት ካልቆመ፣ የምጣኔ ሃብት ማሻሻያው ውጤታማ አይሆንም በማለት ገልፀዋል፡፡ እርምጃው በአዲሱ ዓመት ለውጥ እንዲያመጣ ከተፈለገ፣ መንግሥት ግጭቶችን ለማቆምና በኢኮኖሚው የሚታየውን የአቅርቦት ጉድለቶች ለማስተካከል መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ መክረዋል፡፡
መድረክ / ፎረም