በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፀሐይ ግርዶሽ - ኦገስት 21


ኦገስት 21 / 2017 ዓ.ም. [ከአሥር ቀን በኋላ የፊታችን ነኀሴ 15፤ በወዲያኛው ሰኞ] ዩናይትድ ስቴትስን ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የሚያቋርጥ የፀሐይ ግርዶሽ ይኖራል።

ኦገስት 21 / 2017 ዓ.ም. [ከአሥር ቀን በኋላ የፊታችን ነኀሴ 15፤ በወዲያኛው ሰኞ] ዩናይትድ ስቴትስን ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የሚያቋርጥ የፀሐይ ግርዶሽ ይኖራል።

ያለፈው የፀሐይ ግርዶሽ ዩናይትድ ስቴትስ ምድር ላይ የታየው የዛሬ 38 ዓመት ነበር። እንዲህ ዓይነት ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያቋረጣት ግርዶሽ የነበረው ግን የዛሬ መቶ ዓመት ነበር።

ግርዶሹ በተወሰኑ አካባቢዎች ሙሉ ግርዶሽ (TOTAL ECLIPSE) ሲሆን ከፊል ግርዶሽ (PARTIAL ECLIPSE) ሥር የሚያርፉ ስፋት ያላቸው የዩናይትድ ስቴትስና የካናዳ አካባቢዎች አሉ።

ዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ ከፊል ግርዶሽ ሥር ከሚያርፉት ናቸው።

ግርዶሹ በዋሺንግተን ዲሲ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ ሰባት ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ ላይ ይጀምርና ስምንት ሰዓት ከ42 ደቂቃ ሲሆን ከፍተኛው ከፊል ግርዶሽ ላይ ይደርሳል። ከሰዓት በኋላ አሥር ሰዓት ከ01 ደቂቃ ሲሆን ጨረቃ ከፀሐይ መንገድ ሙሉ በሙሉ ትወጣና በዋሺንግተን ዲሲ የግርዶሹ ፍፃሜ ይሆናል። ጨረቃ ወደ ፀሐይ አንፃር ገብታ ሙሉ በሙሉ እስክትወጣ ሙሉው የግርዶሽ ጉዜ 2 ሰግት ከ44 ደቂቃ ነው የሚሆነው።

ኦገስት 21 ወይም ነኀሴ 15 በአመዛኙ ፀሐያማ፣ ሙቀቱም ከፍተኛው 85 ዝቅተኛው 70 ዲግሪስ ፋረንሃይት በመሆኑ ለዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ ተመልካች እጅግ የተመቸ እንደሚሆን ተተንብይዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለፈው ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ የነበረው በጥቅምት 1952 ዓ.ም. (የዛሬ 57 ዓመት) የነበረ ሲሆን መጭው ደግሞ የሚውለው ዕሁድ፣ መጋቢት 2/215ዐ ዓ.ም. እንደሚሆን ታውቋል።

ለተጨማሪ መረጃና ለባለሙያ ማብራሪያ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የፀሐይ ግርዶሽ - ኦገስት 21
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:57 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG