በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኡጋንድ ውስጥ አንድ ልጅ በኢቦላ በሽታ ሞተ


ኡጋንድ ውስጥ አንድ ልጅ በኢቦላ በሽታ መሞቱ ታውቋል። በኡጋንዳ ጎረቤት ሀገር ኮንጎ ከአንድ ዓመት በፊት ኢቦላ የገባ ሲሆን የድንበር ዘለል ጉዳይ እንደሆነ ተመልክቷል።

የአምስት ዓመት ዕድሜው ህፃን ዛሬ እንደሞተ የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ያስታወቀው ኡጋንዳ ያለው የዓለም የጤና ድርጅት ጽህፈት ቤት ነው።

ህፃኑና በርካታ የቤተሰቡ አባላት ባለፈው ሰኞ ከጎንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ወደ ኡጋንዳ ከገቡ በኋላ የታመመው ልጅ በምዕርብ ኡጋንዳ ወደ ሚገኘው ካጋንዶ ሆስፒታል ተወስዶ እንደነበር የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ጄን ሩት አሴንግ ገልፀዋል።

ሚኒስትሯ አያይዘውም በሀገሪቱ ሦስት የኢቦላ በሽተኞች እንዳሉ አረጋግጠዋል። በሽታው ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እንዳይዛመት ዜጎች ከጤና ባለሥልጣኖች ጋር እንዲተባበሩ ባለሥልጣንዋ ጥሪ አድርገዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG