ዋሺንግተን ዲሲ —
/Regn-eb3 and Mab -114/ የተባሉት መድሃኒቶች ያስገኙት ውጤታማነት ሳይንቲስቶቹ መድሃኒቶቹ ላይ የያዙትን ጥናት አቋርጠው ለአንድ ዓመት በዘለቀው ወረርሺኝ ከ1800 በላይ ሰዎች በሞቱባት በኮንጎ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ላይ እንዲያተኩሩ አድርጓል።
የኮንጎ የሥነ ህይወትና ህክምና (ባዮሜዲካል) ምርምር ብሄራዊ ተቋም ዳይሬክተር ዣን ዣክ ሙዬምቤ “ከእንግዲህ ኢቦላ ተይዞ አለመዳን አከተመ፤ አሁን የተገኘው ስኬት ብዙ ሺዎችን ህይወት ያተርፋል” ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ