በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢቦላ በጊኒ አገረሸ


በምዕራብ አፍሪካ ኢቦላ የተስፋፋባቸው ሃገሮች
በምዕራብ አፍሪካ ኢቦላ የተስፋፋባቸው ሃገሮች

በኢቦላ ክፉኛ ከተጠቁት የምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች መካከል አንዷ የሆነችው ጊኒ ውስጥ ቫይረሱ ቀድሞ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች አዳዲስ ሕመምተኞች እየታዩ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በምዕራብ አፍሪካ ኢቦላ የተስፋፋባቸው ሃገሮች
በምዕራብ አፍሪካ ኢቦላ የተስፋፋባቸው ሃገሮች

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:18 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በኢቦላ ክፉኛ ከተጠቁት የምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች መካከል አንዷ የሆነችው ጊኒ ውስጥ ቫይረሱ ቀድሞ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች አዳዲስ ሕመምተኞች እየታዩ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ሁኔታ ለስድስት ወራት ከተካሄደው የመቆጣጠር ጥረት በኋላ ኢቦላን ጊኒ ውስጥ ማረጋጋት ስለመቻሉ በተሰማው አበረታች ዜና ላይ ቀዝቃዛ ውኃ እንደመቸለስ ታይቷል፡፡ መሆኑም ጊኒ አሁንም በአስቸኳይና በተጠንቀቅ ሁኔታ ላይ ትቆያለች፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በኢቦላ ወደተጠቁ ሃገሮች ይደረጉ የነበሩ በረራዎች እንደተቋረጡና ድንበሮችም እንደተዘጉ መሆን ወደሃገሮቹ ሊደርሱ የሚገባቸውን ሰብዓዊ አቅርቦቶች በወቅቱ እንዳይደርሱ ማድረጉ ተነግሯል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የላይቤርያ መንግሥት ለኢቦላ ወረርሽኝ እየሰጠ ያለውን ምላሽ በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ ገዳቢ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው ሲል የላይቤሪያ ጋዜጠኞች ኅብረት አስታውቋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG