በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ መቆሙን አወጀች

ኮንጎ በቅርቡ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ ቆሟል ስትል አወጀች። ይህ ሊሆን የቻለው በጤና ጥበቃ ባለሥልጣናቷና የዓለም የጤና ድርጅት ፈጣን ርብርብ መሆኑን ገልጣለች።

ኮንጎ በቅርቡ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ ቆሟል ስትል አወጀች። ይህ ሊሆን የቻለው በጤና ጥበቃ ባለሥልጣናቷና የዓለም የጤና ድርጅት ፈጣን ርብርብ መሆኑን ገልጣለች።

ትናንት ማክሰኞ አንድም የበሽታው ተያዥ ሳይገኝ አርባ ሁለት ቀን ሞልቷል።

የዓለም የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሲናገሩ የኮንጎ መንግሥት ቶሎ ምላሽ ሰጥቷል፣ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ፈጥኖ ጠይቋል። “እንዲህ ያለው አመራር ህይወት እንዳይጠፋ ይታደጋል።” ማለታቸው ተጠቅሷል።

ሙከራ ላይ ያለ አንድ የመከላከያ ክትባት ሦስት ሺህ ሰዎችን በቫይረሱ እንዳይጠቁ ሊከላከል መቻሉን አንድ የዓለም የጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ገልፀዋል። ይህም ሆኖ የቅርብ ጊዜው ወረርሺን ሰላሳ ሦስት ሰዎችን ገድሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG