በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ ምስራቃዊ ግዛት ኢቦላ ዳግመኛ ተከሰተ


ሜን ኮንጎ ውስጥ በሚገኝ ማታንዳ ሆስፒታል ውስጥ የኢቦላ ቫይረሰ ታካሚን የሙቀት መጠን የጤና ባለሙያዋ ሲለኩ እኤአ የካቲት 11 2021
ሜን ኮንጎ ውስጥ በሚገኝ ማታንዳ ሆስፒታል ውስጥ የኢቦላ ቫይረሰ ታካሚን የሙቀት መጠን የጤና ባለሙያዋ ሲለኩ እኤአ የካቲት 11 2021

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ግዛት ውስጥ ፣ኢቦላ ለ12ኛ ጊዜ መከሰቱን ፣የአገሪቱ የጤና ሚኒስትር ትናንት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሩ ጄን ጃኩዊ ሙቡንጋኒ ቫይረሱ በሶስት ዓመት ህጻን ላይ መታየቱን ገልጸው፣ ወደ 100 የሚቆጠሩ ሰዎችም ሳይጋለጡ እንዳልቀሩ አመልክተዋል፡፡

እኤአ ከ2018 እስከ 2020 ድረስ በነበረው ወረርሽ በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋበት አካባቢ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ይህ የሆነው ኢቦላ ለመጨረሻ ጊዜ ከታየትበት ከዚህ አካባቢው መጥፋቱ ከተነገረለት አምስት ወራት በኋላ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG