በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢቦላ በኮንጎ


ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ውስጥ በኢቦላ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከሁለት ሺህ መብለጡን የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢቦላ ቫይረስአንድ ሺህ ሦስት መቶ አርባ ስድስት ሰዎች መሞታቸው፣ በታሪክ በኢቦላ ወረርሺኝ በሞቱ ሰዎች ብዛት ሁለተኛ መሆኑ ነው።

የኮንጎ የጤና ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከበሽታው ለማዳን የተቻለው አምስት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ህሙማንን ብቻ መሆኑን ገለጿል።

የፀጥታ ሁኔታው መሻሻሉ ሥርጭቱን ለመቆጣጠር እንዳገዘ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ባወጣው ዘገባ መሰረት አምስት የዕርዳታ ሰራተኞች በአካባቢው ሚሊሽያ ጥቃት ተገድለዋል። የሚኒስቴሩ መግለጫም አሁንም ከባድ ሥጋት ያለ ቢሆንም የዕርዳታ ቡድኖችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶች ጋብ በማለታቸው የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ እንደተቻለ ገልጸዋል።

የኢቦላ ተጠቂዎች ቁጥር ከፍ ማለቱ የሀገሪቱ መንግሥት ምላሹን ገምግሞ ማስተካከል የሚያመለክት ነው ሲል የዓለምቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማኅበራት ፌዴሬሽን አሳስቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG