በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ አፍሪካ የሚጥለው ከባድ ዝናብ አደጋ በማስከተል ላይ ነው


 የአንድ ቤተሰብ አባላት መኖርያቸው በጎርፍ ከተጥለቀለቀባቸው በኋላ አካባቢያቸውን ለቀው ሲሄዱ የሚያሳይ፡ ኦባካ መንደር፣ ኪሱሙ፣ ኬንያ፣ ረቡዕ እአአ ሚያዝያ 17/2024
የአንድ ቤተሰብ አባላት መኖርያቸው በጎርፍ ከተጥለቀለቀባቸው በኋላ አካባቢያቸውን ለቀው ሲሄዱ የሚያሳይ፡ ኦባካ መንደር፣ ኪሱሙ፣ ኬንያ፣ ረቡዕ እአአ ሚያዝያ 17/2024

በምሥራቅ አፍሪካ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በአንዳንድ ሃገራት የጎርፍ አደጋ በማስከተልና ሕይወት በመቅጠፍ ላይ ነው።

በኬንያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ እስከ አሁን ቢያንስ 13 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በታንዛኒያም እየቀጠለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ 58 ሰዎች መሞታቸውን የሃገሪቱ መንግሥት አስታውቋል።

በቀጠናው በርካታ መሠረተ ልማቶች በጎርፉ ሲወድሙ፣ ጎርፍ በሚያሰጋቸው አካባቢዎች ያሉ ሰዎች ለቀው እንዲወጡ ተመክሯል። በርካቶችም መፈናቀላቸው ተነግሯል።

በሃገሪቱ እጅግ ከባድ ዝናብ ስለሚጥል፣ ሕዝቡ ለሚከተለው የጎርፍ አደጋ እንዲዘጋጅ የኬንያው የአየር ትንበያ አገልግሎት አስጠንቅቋል።

በቀጠናው እየታየ ያለው ከባድ ዝናብ፣ በወሩ መጨረሻ የከፋ እንደሚሆን በመጠበቅ ላይ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG