በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምሥራቅ ወለጋው ግድያና የኦሮምያ ክልል መንግሥት አስተያየት


የኦሮምያ ክልል መንግሥት
የኦሮምያ ክልል መንግሥት

ትኩረቱ ሁሉ ሰሜን ኢትዮጵያ ላይ በሆነበት ሰዓት በምስራቅ ወለጋ ከ200 በላይ ንጹሃን በታጣቂዎች መገደላቸውን የገለጹ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪክ ማህበራት መንግሥት በመሰል አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ታጣቂዎች ከሳምንት በፊት በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉት ዜጎች ከ 231 በላይ መሆናቸውን የጠቀሰው እናት ፓርቲ ለምሳሌ ሴቶችና ሕጻናትም እንደሚገኙባቸው አመልክቷል።

"የሸኔ ታጣቂዎች አሳቻ ጊዜ ተጠቅመው ንጹሃንን መግደላቸውን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻም ተናግረዋል-የሟቾቹን ቁጥር ግን አልጠቀሱም።

የኦሮምያ የጸጥታ አካላት ትኩረት በሚሹ የክልሉ አካባቢዎች ዘመቻ ላይ መሆናቸውን እና በታጣቂዎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውንም አቶ ጌታቸው አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሸኔ በሚል በአሸባሪነት ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በማለት የሚጠራው ታጣቂ ቡድን እንደዚህ ዓይነት ውንጀላዎችን ሲያስተባብል ቆይቷል።

የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ የሆኑትን አቶ ጌታቸው ባልቻን አነጋግረናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

የምሥራቅ ወለጋው ግድያና የኦሮምያ ክልል መንግሥት አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:40 0:00


XS
SM
MD
LG