በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቦሰት ወረዳ የሰባት ልጆች እናትን ጨምሮ አራት ሰዎች በመከላከያ አባላት እንደተገደሉ ተገለጸ

በቦሰት ወረዳ የሰባት ልጆች እናትን ጨምሮ አራት ሰዎች በመከላከያ አባላት እንደተገደሉ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00

በቦሰት ወረዳ የሰባት ልጆች እናትን ጨምሮ አራት ሰዎች በመከላከያ አባላት እንደተገደሉ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ውስጥ፣ የሰባት ልጆች እናትን ጨምሮ አራት ሰዎች፣ ባለፈው ሰኞ፣ በመከላከያ ኀይል አባላት እንደተገደሉ፣ ቤተሰቦቻቸው ገለጹ።

ሟቾቹ፣ መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ትደግፋላችኹ፤ ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበር፣ ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የቦሰት ወረዳ ፖሊስ፣ ስለ ግድያ መረጃ እንደሌለው ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ደግም፣ ጉዳዩን የሚያጣሩ መርማሪዎችን ወደ ስፍራው እንደላከ አስታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG