በምሥራቅ ሸዋ ዞን በባቱ እና መቂ ከተሞች፣ በኦሮሞ ነጻነት ተዋጊዎች እና በመንግሥት ኀይሎች መካከል፣ ሰሞኑን እንደጀመረ የተገለጸው የተኩስ ልውውጥ ዛሬም መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ።
የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው የባቱ ከተማ ነዋሪ፣ ካለፈው ሰኞ ምሽት እስከ ትላንት ማክሰኞ ጠዋት፣ በከተማዋ ቀጥሎ የነበረው የተኩስ ልውውጥ፣ ለእንቅስቃሴ መገደብ እና ለአገልግሎቶች መቋረጥ ምክንያት ኾኗል፤ ብለዋል።
በሌላ በኩል፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ምሽት፣ በዚያው በመቂ ከተማ በተፈጸመ ጥቃት፣ አራት የነዳጅ ማደያ ጠባቂዎች ታግተው እንደተወሰዱ ተመልክቷል። በጉዳዩ ላይ፣ ከመንግሥት አካል ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡
ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም