በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጎሮ ዶላ ወረዳ የዳግም አደረጃጀት ተቃውሞ 12 ተማሪዎች መታሰራቸው ተገለጸ


በጎሮ ዶላ ወረዳ የዳግም አደረጃጀት ተቃውሞ 12 ተማሪዎች መታሰራቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:59 0:00

በጎሮ ዶላ ወረዳ የዳግም አደረጃጀት ተቃውሞ 12 ተማሪዎች መታሰራቸው ተገለጸ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ ከጉጂ ዞን ወደ ዐዲሱ ምሥራቅ ቦረና ዞን ባካለለው ጎሮ ዶላ ወረዳ፣ ከ2016 ዓ.ም. የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ጋራ በተያያዘ በተነሣ ተቃውሞ፣ 12 ተፈታኞዎች መታሰራቸውን፣ የትምህርት ቤት ጓደኛቻቸው ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ የታሰሩት፣ ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. የተሰጠው ፈተና፣ አዲስ በተቋቋመው የምሥራቅ ቦረና ዞን ስም መሰጠቱን በመቃወማቸው እንደኾነ ገልጸዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው በወረዳዋ ከተማ ሐራ ቀሎ የሚገኙ ነዋሪዎች፣ አብረዋቸው የነበሩ ተማሪዎች፣ መምህራንና የተማሪ ወላጆች ጭምር መታሰራቸው ስጋት እንደፈጠረባቸውም ጠቁመዋል።

በጉዳዩ ላይ፣ ከጎሮ ዶላ ወረዳ አስተዳደር እና ከትምህርት ጽ/ቤት፤ ከምሥራቅ ቦረና ዞን አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG